300 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በትምህርት ዘ...

image description
- In አስተዳደር ዘርፍ    0

300 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በትምህርት ዘርፍ መንግስት ባመቻቸላቸው ዕድል በ6 ማኅበራት ተደራጅተው ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ


ባለፉት የለውጥ ዓመታት በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱ አርሶ አደሮችን መልሶ በማቋቋም እና በቀጣይም የከተማው ልማት አካታችነቱን ጠብቆ አርሶ አደሩ አብሮ እንዲለማ በርካታ ሥራዎች ተሰርቷል፡፡


ከነዚህ የልማት ሥራዎች አንዱ በመሆነው የትምህርት ዘርፍ በአቃቂ ቃሊቲና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች 2 ትምህርት ቤቶችን በመገንባትና ግብዓት በማሟላት 300 አርሶ አደሮች በ6 ማኅበራት ተደራጅተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል፡፡


ለውጡ ያመጣላቸውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በቅርበት እየተከታተላቸው በዘርፉ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ እጅግ ተመራጭ እና ወደ ኢንቨስትመንት ዘርፍ እየተሸጋገሩ ያሉ ውጤታማ ማህበራት መሆን ችለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments