17,627 አርሶ አደሮች በግል ይዞታቸው ላይ እንዲያለሙ ተደርጓል፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
17,627 አርሶ አደሮች በግል ይዞታቸው ላይ እንዲያለሙ የተደረገ ሲሆን ካላቸው ይዞታ ላይ አነስተኛ ቦታ ያላቸው 80 በመቶ እንዲያለሙ እንዲሁም ሰፊ ይዞታ ካላቸው 20 በመቶ ይዞታቸውን ለከተማ ግብርና ስራ እንዲያውሉ በማድረግ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን ሰፊ ሥራ ተሰርቷል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በከተማ ግብርና ተሳታፊ ከሆነው 1.2 ሚሊዮን ተጠቃሚ ውስጥ ከተገኘው 478,567.18 ቶን ምርት አርሶ አደሩ በተሰማራበት ስራ ከራስ ፍጆታ አልፎ የገበያ ማረጋጋት ስራ ላይ ከፍተኛ ድርሻ አበርከተዋል፡፡
በሌላ በኩል በግል ይዞታቸው ላይ ሰፊ የልማት ሥራ ማከናወን የሚችሉ 168 አርሶ አደሮች ወደ ኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሸጋገሩ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር ተችሏል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments