ከ4,848 በላይ ተጠቃሚዎችን በፋሚሊ ቢዝነስ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
የከተማ ግብርና በቤተሰብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በከተማና በሀገር ደረጃም የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ የከተማ ልማትን ለማምጣት ወሳኝ መሳሪያ ነው።
በ2018 በጀት ዓመት በባለፈው 10 ወራት 4,848 የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን በፋሚሊ ቢዝነስ እንዲሁም 120,971 አዲስ የቤተሰብ ፍጆታ ተጠቃሚዎችን ወደዘርፉ ማስገባትና ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ መሆኑን የእንስሳት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ደጀኔ ጌታቸው ገልፀዋል፡፡
ሌላው ዶ/ር ደጀኔ 334,026 ነባር በእንስሳት ዘርፍ የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን የግብዓትና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ሙያዊ እና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ማስቀጠል መቻሉን አያይዘው አንስተዋል፡፡
በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ለተሰማሩ ተጠቃሚዎች ከ2,553,298 በላይ የተለያዮ ግብዓቶችን፣ 140,123 አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና 2,023 ኢ.ኤም ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ መደረጉንም ዳይሬክተሩ አያይዘው አንስተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments