ዜና ትንታኔ

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ዜና ትንታኔ

የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን መልሶ የማቋቋምና የማልማት ሥራ በስፋት ተሰርቷል፡፡


አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ


ባለፉት 7 የለውጥ ዓመታት በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱ አርሶ አደሮችን መልሶ በማቋቋም እና በቀጣይም የከተማው ልማት አካታችነቱን ጠብቆ አርሶ አደሩ አብሮ እንዲለማ በርካታ ሥራዎች ተሰርቷል፡፡

የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ምዝገባ፦ በልማት ምክንያት የተነሱ 45,527 አርሶ አደሮችና የአርሶ አደር ልጆችን በሦስት ዙር የመለየትና የመመዝገብ ሥራ ተከናውኗል።

የጋራ ኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት አቅርቦት፦ በከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ መሠረት ለ22,915 ልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የማስተላለፍና የማስረከብ ሥራ ተሰርቷል።

የጋራ ኮንዶሚኒየም ንግድ ሱቆች ስርጭት፦ በማኅበር ለተደራጁ ልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ 233 የጋራ መኖሪያ ሱቆች ተላልፈዋል።

የአቅም ግንባታ ሥልጠና፦ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ 1,243 ማኅበራትና 6,782 አባላት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በኩል ተግባራዊ ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል።

የፋይናንስ፣ የቦታና የማሽነሪ አቅርቦት ድጋፍ፦ የከተማ አስተዳደሩ ብር 985,066,704.99 በጀት በመመደብ ለ5,426 በልማት ምክንያት ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች በ742 ማኅበራት በማደራጀት የመሥሪያ ቦታ፣ የፋይናንስ/ቀጥታና ተዘዋዋሪ ብድርና የማሽነሪ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ከተደረገው አጠቃላይ ድጋፍ ውስጥም በአዲስ ካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ በኩል የተገዙ የተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች (አይሱዙ መኪና፣ ፍሪጅ፣ ሚዛን እና የተለያዩ መሣሪያዎች) በማኅበር ለተደራጁ 156 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ተላልፈዋል።

ቀጥታ ሰብአዊ ድጋፍ፦ ምንም ገቢ ለሌላቸውና መሥራት ለማይችሉ 1,648 ቀጥታ ድጋፍ ፈላጊ አርሶ አደሮች ለምግብ ፍጆታና ለመጠለያ የሚሆን 312,318,460.00 ብር ድጋፍ ተደርጓል።

የትምህርት ቤት ግንባታና የሥራ ዕድል፦ በአቃቂ ቃሊቲና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች 2 አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን በመገንባትና ግብዓት በማሟላት 300 አርሶ አደሮች በ6 ማኅበራት ተደራጅተው ወደ ሥራ ገብተዋል።

የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል፦ በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 10 በ14 ሄክታር ላይ የተገነባው ማዕከል የወተት፣ የከብት ማደለቢያ፣ የዶሮ እርባታ፣ የመኖ ማቀነባበሪያና 32 ሱቆችን በማሟላት 104 ማኅበራትንና 540 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ተደርጓል።

የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፦ በልማት አካባቢዎች የሚገኙ 7,047 አርሶ አደሮች አስተማማኝና ንጹህ የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments