ዕቅድን የሥራ መመሪያ አድርጎ የላቀ አፈፃፀም ማ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ዕቅድን የሥራ መመሪያ አድርጎ የላቀ አፈፃፀም ማስመዝገብ የሁሉም ግብ ነው፡፡

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 02 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


የግንቦት ወር ተግባራት አፈፃፀም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የተያዘውን እቅድ ያሳካና የዓመቱ ውጤታማ ስራ አፈፃፀም ማሳያ ነው፡፡
 
በእንስሳት ሃብት ልማት ሥራ ዘርፍ የተጠቃሚውን ኢኮኖሚ ለማሻሻል በፋሚሊ ቢዝነስ የተሰሩ ስራዎች የተሻለ አፈፃፀም የተገኘባቸው መሆኑን የኮሚሽኑ የ11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያመለክታል፡፡ ነባር የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን ከማስቀጠል አንፃር (90%) ውጤት የተመዘገበበት መሆኑም በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
 
ከእርግዝና ምርመራና ከማዳቀል አገልግሎት አንፃርም በእርግዝና ምርመራ ከእቅድ በላይ የተከናወነ ሲሆን በማዳቀል አገልግሎት የጥጆች ውልደት ልዩ ትኩረት በመስጠት መስራት የሚገባ መሆኑን ከሪፖርቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
በእፀዋት ሃብት ልማት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አንፃር በንጥረ ነገር ይዘታቸው የበለፀጉና የተቀናጀ ግብርና ምርት እንዲመረት በማድረግ ማህበረሰቡ የአመጋገብ ሥርዓቱን እንዲያሻሽል መደረጉ በስከት ተነስቷል፡፡
 
በ11 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የጓሮ አትክልትና የፍራፍሬ ስርጭትን አስመልክቶ ከ100% በላይ ተፈፃሚ ሲደረግ የእንጉዳይ ዘር ስርጭት 86.4% ተፈፃሚ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
 
ከሬጉላቶሪ ሥራዎች አፈፃፀም አንፃር በቅድመና ድህረ እርድ ምርመራ ስራ ከተያዘው እቅድ 87.3% የተፈፀመ ሲሆን የተያዘውን እቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የእርድ እንስሳት በታቀደው ልክ ወደ ቄራ ያለመምጣት ውስንነት መኖሩ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
 
አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት በተያዘው እቅድ 102% ከእቅድ በላይ ተፈፃሚ ሲሆን የብቃት ማረጋገጫ በወሰዱ 182 ድርጅቶች ላይ የቁጥጥር ሥራ 100% ማከናወን መቻሉ ተጠቅሷል፡፡
 
ከአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት አንፃርም በመልሶ ማቋቋም የዘላቂ ቀጥታ ድጋፍ 100% ተፈፃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን አርሶ አደሮች በ20/80 በራስ ይዞታ ማልማት፣ ወደ ኢንቨስትመንት ለሚገቡ ሁኔታዎችን የማመቻቸት፣ በማህበር ተደራጅተው ወደ ሥራ የገቡት ላይ ኦዲት ሥራ እና ድጋፍን ክትትል የማድረግ ተግባራት በከፍተኛ ውጤት የተከናወኑ መሆኑ በኮሚሽኑ የ11 ወራት ሪፖርት ላይ ተገልጿል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments