እንስሳት ሃብት ልማት ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
ከቤተሰብ ፍጆታ አንፃር በተከናወኑ ሰፋፊ ሥራዎች የተሳታፊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በዚህ በጀት ዓመት ብቻ በ11 ወራት ውስጥ 120,971 ተጠቃሚዎች ከዘርፉ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡
የቤተሰብ ገቢ ማሻሻያ (Family Business) በቅርብ ጊዜ የተጀመረ ቢሆንም በሁሉም ክፍለ ከተማ ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡
ከዚህ ቀደም በቤተሰብ ፍጆታ ብቻ ተወስነው የነበሩ ተጠቃሚዎችን ወደ ቤተሰብ ገቢ ማሻሻያ ተግባራት በማሳተፍ የገቢ ምንጫቸውን እንዲያስፋፉና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ ተችሏል። በ2018 በጀት ዓመት በ11 ወራት ውስጥ 4,848 ተጠቃሚዎችን በዘርፉ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
በባለፉት አምስት ዓመታት (2014 - 2018 ዓ.ም) በእንስሳት ሃብት ልማት ቴክኖሎጂን መሰረት አድርጎ በተሰሩ ስራዎች 74,530 ለሚሆኑ ሴቶችና ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር የተቻለ መሆኑን ከእንስሳት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሥርዓት እያደገ መምጣት የምርት ወጪን በመቀነስ፣ የሥራ ቅልጥፍናን በማሳደግ እና የምርት ዕድገትና ጥራትን በማሻሻል ለተጠቃሚዎች የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ አድርጓል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments