“ሰውን ሰው ያደረገው ሥራና ሥራ ብቻ ነው!፡፡”...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

“ሰውን ሰው ያደረገው ሥራና ሥራ ብቻ ነው!፡፡” አቶ ሞገስ ባልቻ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በቤተሰብ 400 በተጠቃሚ ከ2,000 በላይ ለሆኑ በፋሚሊ ቢስነስ ለተደራጁ የከተማችን ነዋሪዎች የግብርና ኤክስቴንሽን ማጠናከሪያ እና የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ የግብዓት ስርጭት አድርጓል፡፡    


በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ ሰውን ሰው ያደረገው ሥራና ሥራ ብቻ በመሆኑ በከተማ ግብርና ሥራ ላይ የተሰማራችሁና ወደፊትም ወደ ዘርፉ የምትገቡ በቁርጠኝነት ሰርታችሁ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ድህነትን ታሪ ማድረግ ይገባናል ብለዋል፡፡


በም/ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በበኩላቸው የከተማ ግብርና በርካቶችን “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” ያሸጋገረ በተግባር የሚታይ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ለአራት ዓመት የተቀመጠውን የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር በስኬት በማጠናቀቅ ዛሬ ደግሞ ለ400 በቤተሰብ ገቢ ማስገኛ ለተደራጂ 2,000 ተጠቃሚዎች ከ17,000 በላይ እንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮዎች፣ 400 ዘመናዊ የዶሮ ኬጂ፣ 400 ኩንታል የተቀነባበረ የዶሮ መኖ፣ 5,000 ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች፣ 30 የውሃ ሞተር ፓምፕ እና 10 ሞተሮች ስርጭት መደረጉን ተናግረዋል፡፡


አያያዘውም በያዝነው በጀት ዓመት ብቻ በ4 ዙር የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ መርሃ-ግብር 135,992 የሚሆን ባለአምስት እና ባለ ሃምሳ ዶሮ ኬጂ፣ ከ824,959 ኩንታል በላይ የተቀነባበረ መኖ፣ ከ2,487,989 በላይ ቄብ ዶሮዎችን ከፍተኛ ቁጥር ላላቸው የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎች ተደራሽ መደረጉን ገልፀዋል፡፡


ለበለጠ መረጃ፡-
 YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
 Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
 Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
 Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments