“ተስፋን እንትከል!፡፡”

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

“ተስፋን እንትከል!፡፡”


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አጠቃላይ አመራርና ሰራተኞች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የፍራፍሬ ችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡
 
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ዛሬ እየተከልን ያለው የፍራፍሬ ችግኝ ከአረንጓዴ ልማትነቱ ባሻገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሰራን ያለው የመደበኛ ሥራችን አካል ነው ብለዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ለምግብነት የሚሆኑ እና የጥላ ዛፍ 1,500 ችግኞችን መትከል ተችሏል፡፡
 
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተከኙት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን አስፋው የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን ለማኖር በወረዳው በመገኘታቸው አመስግነው ወረዳው የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የተተከሉት ችግኞች የፍራፍሬ ችግኞች በመሆናቸው ከውበትነት ባለፈ ለምግብነት የሚውሉ በመሆኑ ተገቢው እንክብካቤ እንደሚደረግ በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መሃመድ ልጋኒ ገልፀዋል፡፡

በችግኝ ተከላ ሂደቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞችም በዛሬው ዕለት የተካሄደው ተከላ በዓይነቱ የተለየ እና በቀጣይ ለመንከባከብም ምቹ በመሆኑ በአግባቡ እንከባከባለን ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments