“ችግኝ መትከል ለእኛ ለግብርና ቤተሰብ ባህል ነው!፤” አቶ ባዮ ሽጉጤ፡፡
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አጠቃላይ አመራሮችና ሰራተኞች “ተስፋን እንትከል!” በሚል መሪ ቃል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ግቢ ውስጥ 2,000 የፍራፍሬ ችግኝ ተካላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ዓላማ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ህይወት የተመቸች፤ ጽዱና አረንጓዴ የመኖሪያ ሥፍራን የተጎናጸፈች፣ የአየር ንብረቷ ለሰው ልጅ ለኑሮ ተስማሚ የሆነች ሀገር እንድትሆን ድርሻው የማይተካ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ ዓመታት በስኬታማነት በመካሄድ ላይ መሆኑንም ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ገልፀዋል።
የአረንጓዴ አሻራ ማኖር ታላቁ ዓላማችን ስንደርስበት ለመኖር ሳይሆን እየኖርነው የምንደርስበት መሆናችንን በተግባር ለዓለም አረጋግጠናል። ምክንያቱ ደግሞ አረንጓዴ አሻራ የምናወራው ሳይሆን የምንኖረው በመሆኑ ነው፡፡
የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞችም በየዓመቱ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብና በተግባር ለጥቅም ማድረስ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የችግኝ ተከላ ዓመት ጠብቆ የሚመጣ ተግባር በመሆኑ እጅግ በጣም የሚጓጉለት እንደሆነና በተከላው መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments