የተፈጥሮ ማዳበሪያ የአፈር ለምነትን በማሻሻል ረገድ የማይተካ ሚና አለው፡፡
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
የተፈጥሮ ማዳበሪያ (እንደ ኮምፖስት እና ቦካሽ) የእጽዋትና የእንስሳት ተረፈ ምርቶች በአፈር ውስጥ በሚገኙ ጥቃቅን ህዋሳት (ማይክሮ ኦርጋኒዝሞች) ተብላልቶ የሚዘጋጁ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር ነው።
የተፈጥሮ ማዳበሪያ የአፈርን እርጥበት እና ለምነት በመጠበቅ፣ ከፍተኛ የምርት እድገት ለማምጣት እና የወጪ ቅነሳ ለማድረግ ያግዛል፡፡
የተፈጥሮ ማዳበሪያን በብቃት ለማዘጋጀት የማዘጋጃ ቁሳቁሶች፡ (የእንስሳት ኩስ፣ የደረቁ ቅጠሎች፣ ገለባ፣ የእንቁላል ቅርፊት እና የቀሩ የፍራፍሬ/አትክልት ልጣጮች መጠቀም እንደሚቻል የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
አዘገጃጀቱን በተመለከተም እነዚህን ተረፈ ምርቶች በደረጃ (Layer) በመደርደር፣ አየር እንዲገባ በማድረግ እና አስፈላጊ ከሆነም ውሃ በመርጨት መበስበሱን መጠበቅ ይገባል ይላሉ።
ፈሳሽ ማዳበሪያ መጠቀም እንደሚቻል በየክፍለ ከተማው ተዘዋውረን የተመለከትነው እውነታ ያስረዳል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments