ግብርናችን ለከተማችን ነዋሪዎች ያስገኘው ውጤት...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ግብርናችን ለከተማችን ነዋሪዎች ያስገኘው ውጤት ምንድነው?

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ


የከተማ ግብርና የኑሮ ውድነትን በማቃለል፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ እና ለነዋሪዎች አረንጓዴ አካባቢን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ይህ ዘርፍ በተለይ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ውስጥ ወጪን በመቀነስ የራሳቸውን የምግብ ፍላጎት በራሳቸው አቅም እንዲሸፍኑ አድርጓል።

የከተማ ግብርና ለነዋሪዎች ያስገኛቸው ዋና ዋና ውጤቶች

> የምግብ ዋስትና እና ጤናማ አመጋገብ፡ ነዋሪዎች እንደ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ እንቁላል እና የወተት ተዋጽኦዎች ያሉ ትኩስ የግብርና ውጤቶችን በቅርብ በማግኘታቸው የሥርዓተ ምግብ እና የምግብ ዋስትናቸውን እያረጋገጡ ይገኛሉ።

> የኑሮ ውድነት ቅነሳ፡ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የዕለት ተዕለት የቤት ወጪያቸውን በከፊልም ቢሆን ለመሸፈን አስችሏቸዋል።

> የሥራ ዕድል ፈጠራ፡ በተለይም በከተሞች ውስጥ ላሉ ወጣቶች እና ሴቶች በዕርባታና እጽዋት (አትክልት) ልማት ላይ በመሰማራት የስራ ዕድል ፈጥሯል።

> የአካባቢ ጥበቃና ውበት፡ ከተሞችን ፅዱና አረንጓዴ በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።

> የከተማ ግብርና እንዴት እንደሚካሄድ እና ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው የበለጠ ለመረዳት በተለይ በመዲናችን አዲስ አበባ ላይ እየተሰራ ያለው የከተማ ግብርና ሥራ በእጅጉ ለብዙዎች አስተማሪ እየሆነ ይገኛል፡፡

> የገቢ ምንጭ መሆኑ፡ ከተማ ግብርና በአሁኑ ጊዜ የዝቅተኛው ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን የባለ ሃብቶችም ጭምር የኢንቨስትመንት አማራጭ እና የገቢ ምንጭ እየሆነ የመጣ አትራፊ የግብርና ኢንዱስትሪ ወይም ዘርፍ ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments