ፕሬስ ሪሊዝ

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ፕሬስ ሪሊዝ

አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን
ስ.ቁ 011-65-91-168                       
E-mail፡ farmeragr2020@gmail.com
  
                     


                                                                        
ፕሬስ ሪሊዝ



አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አርሶ አደሮች ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ እና የከተማ ግብርና ልማት እንዲስፋፋና እንዲዘምን ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ኮሚሽኑ በአዋጅ ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል አንዱ የግብርና ምርትና አገልግሎት ጥራት፣ ሃይጅንና ደህንነት ተጠብቆ ለማህበረሰቡ እንዲቀርብ ማድረግ ነው፡፡
ይህንን ኃላፊነት ለመወጣትም ተቋሙ ከራሱ ከማዕከል እስከ ወረዳ ካለው መዋቅር፣ ከሚመለከታቸው ቅንጅታዊ ተቋማት እና አጠቃላይ የግብርና ቤተሰብ ጋር በመሆን ውጤት ተኮር የሆነ በመርህ ላይ የተመሰረተ ሥራ ይሰራል፡፡ ሥራዎቹንም በየጊዜው እየገመገመ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ክፍተቶችን ደግሞ ፈጥኖ እያረመ የሚጠበቅበትን ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ኮሚሽኑ የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ግምገማ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም የማዕከል አመራሮች፣ የዘርፉ የክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ቡድን መሪዎች፣ የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የማዕከል ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች በተገኙበት ጉርድ ሾላ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋናው መስሪያ ቤት አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይቱ ያካሂዳል፡፡
ስለሆነም የማዕከል አመራሮች፣ የዘርፉ የክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ቡድን መሪዎች፣ የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች የማዕከል ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ከጥዋቱ 2፡30 ሰዓት በተጠቀሰው ቦታ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ ለወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በክፍለ ከተማ በኩል ጥሪ እንዲተላለፍላቸው ኮሚሽኑ ያሳስባል፡፡
                                                         ኮሚሽኑ!
 ለበለጠ መረጃ፡-
 YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
 Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
 Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
 Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments