ሥራ ነው ሰውን ሰው ያደረገው!፡፡ አባ ኤልያስ

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ሥራ ነው ሰውን ሰው ያደረገው!፡፡ አባ ኤልያስ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም


በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሃያት ጣፎ ታቦር ሰፈር ኮንደምንየም ነዋሪ የሆኑት አባ ኤልያስ በጋራ መኖሪያ ኮንደምንየሙ ግቢ ውስጥ ያለውን ክፍት ቦታ በመጠቀም የከተማ ግብርና ሥራዎችን አርአያነት ባለው መንገድ ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡


አባ ኤልያስ ፈጣሪ “ለፍተህ ጥረህ ግረህ ብላ” አለ እንጅ ሰርቶ መብላት ኃጢያት ነው ብሎ አላስተማረም፤ በመሆኑም የጋራ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ክፍት ቦታ በመጠቀም የግብርና ሥራዎችን ሰርተን ለቤት ፍጆታ ከመጠቀም ባለፈ ለአእምሯችን ምግብ አግኝተንበታል ብለዋል፡፡


በጋራ መኖሪያ ቤት ኮንደምንየም ግቢ ውስጥ አባ ኤልያስ የተለያዮ የግብርና ሥራዎችን ማለትም የተለያዮ አትክልቶች (ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ ጎመን፣ ቃሪያ፣…)፣ የተለያዮ ፍራፍሬዎቸ (ማንጎ፣ አቦካዶ፣ ፓፓያ፣ …)፣ የንብ ማነብ ሥራ፣ ችግኝ ማፍላት፣ የእንስሳት መኖ የሚሆን ሳር ልማት እና የኮምፖስት ዝግጅት በአርአያነት እየተገበሩ መሆኑን ተመልክተናል፡፡


የሚገኘውንም ምርት ከራሳቸው ባለፈ በአብዛኛው ለአካባቢው ማህበረሰብ በነፃ እየሰጡ መሆኑን በቦታው ያገኘናቸውና ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀውልናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሥራቸው ወደ ሌሎች እየሰፋ እንደሆነና የእሳቸውን አርአያነት እየተከተሉ መሆኑን በአካባቢው ያገኘናቸው የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments