
ከሸማችነት ወደ አምራችነት!
አዲስ አበባ፤ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም
የብልጽግና ፓርቲ 2ኛው መደበኛ ጎባኤን አስመልክቶ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ የፓርቲው አባላት በእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል ተገኝተው እስከ 5:45 ሰዓት በሦስት ዙር ጉብኝት አድርገዋል።
ኮሚሽኑም እንግዶቹን በተደራጀ መንገድ በመቀበል የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ያፈራውን እርጎ፣ እንቁላ እና የግብርና ምርት የሆነውን ዳቦ ቁርስ በማዘጋጀት ሁለቱን ዙር ያስተናገደ ሲሆን ለሦስተኛው ዙር የማዕከሉ ምርት የሆነውን ሰንጋ በማዘጋጀት ምሳ ለማብላት እየተጠባበቀ ይገኛል።
በጉብኝቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላትም እጅግ መልካም ነገር በማዕከሉ የተመለከቱ መሆኑን በየዙሩ አንስተዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments