ግብርና እና ሥርዓተ-ምግብ፡ ለጤናማ ትውልድ!
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
ግብርና ሰብልና የእንስሳት ተዋጽኦ ማምረት ብቻ ሳይሆን የኅብረተሰብን የጤና እና የሥርዓተ-ምግብ ዋስትና የሚያረጋግጥ ዋና መሠረት ነው።
በግብርና ምርት እና በተመጣጠነ ምግብ መካከል ያለው ዝምድና በቀጥታ የተያያዘ ነው፤ የምንመገበው ምግብ ጥራት፣ ዓይነት እና ብዛት የሚወሰነው በማህበረሰቡ አጠቃላይ የግብርና እንቅስቃሴ (ምርትና ምርታማነት) ነው።
ዓይነተ-ብዙ እና የተመጣጠነ የግብርና ምርት ሲኖር የማህበረሰቡ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ይረጋገጣል። ከተለያዩ የእህል ዓይነቶች በተጨማሪ አትክልትና ፍራፍሬዎችን፣ ጥራጥሬዎችን እና የእንስሳት ተዋፅኦዎችን አጣጥሞ ማምረት የቪታሚን እና የካሎሪ እጥረቶችን ለመቅረፍ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
በሌላ በኩል፣ ሥርዓተ-ምግብን ያማከለ የግብርና ዘይቤን መከተል የመቀጨጭ፣ የደም ማነስ እና ሌሎች ከተመጣጠነ ምግብ እጥረት ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮችን ለመቀነስ ያስችላል።
በአጠቃላይ፣ የግብርናው ክፍለ-ኢኮኖሚ ከምግብ ብዛት ባሻገር ለምግብ ጥራት ትኩረት ሲሰጥ፣ ጤናማ እና አምራች ህብረተሰብ መገንባት ይቻላል።
ለዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የከተማ ግብርናን በማስፋፋት፣ በማጠናከርና በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ከመቸውም ጊዜ በላይ በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ሥራ እየሰራ ይገኛል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments