ግብርና «ሰው ተኮር» ነው!፡፡
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
ግብርና «ሰው ተኮር» ነው ሲባል ትኩረቱ ሰብልና እንስሳት ማራባት ወይም ምርት ማሳደግ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በነዚህ ሂደቶች ውስጥ የሰውን ልጅ ህይወት፣ ደህንነት እና እድገት ማዕከል ያደረገ ነው ማለት ነው።
የምግብ ዋስትና እና ጤና፡- ዋና አላማው የሰውን ልጅ ከራብ ማዳን፣ የተመጣጠነ ምግብ ማቅረብ እና ጤናማ ትውልድ መገንባት ላይ ያተኮረ ነው።
የስራ እድል እና የኑሮ ማሻሻል፡- በአርሶ አደሩ እና በግብርና ዘርፍ በሚተዳደሩ ዜጎች ገቢ እድገት፣ በሴቶችና ወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ እንዲሁም በህብረተሰቡ የኑሮ ደረጃ መሻሻል ላይ ትኩረት መስጠቱ ነው።
የሰብአዊ መብት እና እኩልነት፡- የአርሶ አደሮችን፣ የግብርና ዘርፍ ተጠቃሚዎችን፣ የሴቶችን እና የወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማረጋገጡ (የመሬት ስሪት፣ የብድር እና የቴክኖሎጂ ተዳራሽነትን ጨምሮ) የሚሰራ መሆኑ ነው።
የእውቀት እና ባህል ጥበቃ፡- የሀገር በቀል እውቀቶችን፣ ባህላዊ የአመራረት ዘዴዎችን እና የአካባቢውን ህብረተሰብ ፍላጎት ያከበረ ልማት ማካሄዱ ነው።
ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ አካባቢ፡- የአርሶ አደሩን እና በግብርና ሥራ ዘርፍ የተሰማሩትን አቅም የሚገነቡ፣ ድካምን የሚቀንሱ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ከፀረ-ተባይ መድሃኒቶችና ከባድ ስራዎች የሰውን ደህንነት መጠበቅ ላይ ትኩረት መስጠቱ ነው።
ባጭሩ ግብርና ሰው ተኮር ነው ሲባል «ምርት የሚመረተው ለሰው ልጅ ነው፤ የምርቱም ባለቤትና ተጠቃሚው ሰው ነው» የሚለውን መርህ መከተል ማለት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments