2018/19 ምርት ዘመን 7,165 ሄክታር መሬት በመኸር ሰብል የሚሸፈን ይሆናል፡፡
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም
የ2018/19 ምርት ዘመን የመኸር ሰብል ልማት ሥራዎች በታቀደው ልክና በበቂ ዝግጅት እየተከናወኑ መሆኑን ያነጋገርናቸው በአርሶ አደርና ከተማ ግበርና ልማት ኮሚሽን በእጽዋት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ አግሮኖሚስት የሆኑት አቶ ተስፋዬ ኪ/ማርያም ገልፀዋል፡፡
አቶ ተስፋዬ እንደ ከተማ 7,165 ሄክታር መሬት በመኸር ሰብል ልማት የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በማስፋፊያና በሰብል አምራች ወረዳዎች ለሚገኙ 764 ሞዴል አርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኒኮች ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥልጠና መሰጠቱንም ባለሙያው ጠቅሰዋል፡፡
ሌላው ምርጥ ዘር እና ሰው ሠራሽ የአፈር ማዳበሪያ ከአምናው በተሻለና በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እንዲሆን በበቂ ሁኔታ መሰራቱና በግብዓት እጥረት ዙሪያም ምንም ዓይነት ችግር እንዳልተከሰተ አንስተዋል።
አርሶ አደሮች የእርሻ ማሳ ዝግጅታቸውን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲጠቀሙ በተሰጠው ግንዛቤ መሠረት ቦሌ፣ ለሚ ኩራ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ 413 ሞዴል አርሶ አደሮች መሬታቸውን በበቂ ሁኔታ በትራክተር አርሰው ዘር እየዘሩ መሆኑን በመስክ ምልከታችን መመልከት ተችሏል፡፡
እስካሁን በማስፋፊያ ክፍለ ከተሞችና በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተደረገው የመኸር ሰብል ዘር 45 ሄክታር ስንዴ እና 31 ሄክታር ጤፍ በባለሙያ ታግዞ በ125 አርሶ አደሮች አማካኝነት በመስመር መዘራቱን አቶ ተስፋዬ ኪ/ማርያምተናግረዋል፡፡
ቴክኖሎጂን ከመጠቀም ባለፈ የሴቶችና የወጣቶች ተሳትፎ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በተለይ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የተለያዩ ክፍት ቦታዎችን በማልማት ምርትና ምርታማነት
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments