የግብርና ምርቶች ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የግብርና ምርቶች ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ የተጠናከረ ቁጥጥርና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ


ህብረተሰቡ የሚጠቀማቸው የግብርና ምርቶች ለጤና ተስማሚና ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ጥብቅ የጥራትና ደህንነት ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል።


በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ የሐምሌ ወር ሥራ እንቅስቃሴ እንደሚያመለክተው የግብርና ምርቶች ጥራታቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ እየሰራ ይገኛል፡፡


በሌላ በኩል የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ የመኸር ሥራ እንቅስቃሴ እንደሚያሳየው የ2018/19 ምርት ዘመን የመኸር እርሻ ሥራን አስመልክቶ በፀረ-ተባይ እና ማዳበሪያ አጠቃቀም ላይ ለአርሶ አደሮች አስቀድሞ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በስፋት እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡


የምርት ደህንነትንና ጥራትን የሚያረጋግጡ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች በየደረጃው ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር እየተሰራ ይገኛል፡፡


ከመኸር እና ድህረ-መኸር ብክነት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ አላስፈላጊ ብክለቶችን ለመከላከልም የሚያስችሉ ዘመናዊ አሰራሮች እየተተገበሩ ይገኛሉ።


ይህ ሥራ የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቁ ባሻገር፣ የከተማችን የግብርና ምርቶች በገበያ ላይ ያላቸውን ተወዳዳሪነትና ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments