ሬዲ ማይት (Red Mite / Dermanyssus gallinae) በዶሮ እርባታ ላይ ከባድ ኢኮኖሚያዊ እና የጤና ጉዳት የሚያደርስ ደም መጣጭ ተባይ (Parasite) ነው።
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
ይህ ተባይ ዶሮዎችን እንዴት እንደሚያጠቃና አደገኛነቱን የሚያሳዩ ዋና ዋና ነጥቦች ጥቃቱን የሚያደርስበት መንገድ ተባዩ ቀን ቀን በዶሮው መኖሪያ ግድግዳ ስንጣቂ፣ እንጨትና ጎጆዎች ውስጥ ይሸሸጋል። ማታ ማታ ግን ከሸሸገበት በመውጣት የተኙ ዶሮዎች አካል ላይ በመውጣት ደማቸውን ይመጣል።
የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ከፍተኛ ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ከበደ ፈጣን እና ከፍተኛ የመራባት አቅም ያለው በሞቃት ወቅት በጥቂት ቀናት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሆነው ስለሚራቡ ሙሉውን የዶሮ ቤት በፍጥነት ይወሩታል ሲሉ ገልፀዋል።
እንደ ዶ/ር ታደሰ ከበደ ገለፃ ተባዮ የደም ማነስ (Anemia) እና ሞት፣ የእንቁላል ምርት መቀነስ፣ በሽታ አስተላላፊነት፣ የዶሮዎች በሽታ መከላከል አቅም መዳከም በተለይም በእረፍት ማጣት እና በደም ማነስ ምክንያት የዶሮዎቹ በሽታ የመከላከል አቅም ስለሚወርድ ለሌሎች ተጨማሪ በሽታዎች ያጋልጣቸዋል።
ሐኪሙ ምልክቶችንም በተመለከተ ዶሮዎች ማታ ማታ ማረፍ አለመቻል፣ ክንፋቸውን ማጨብጨብና እራሳቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ማከክ፤ የዶሮዎቹ አፉጫና የጭንቅላት ቆብ (Comb) ፈዝዞ ነጭ የመሆን አዝማሚያ ማሳየት (የደም ማነስ ምልክት) እና በዶሮው ቤት ግድግዳዎች፣ እንጨቶች ወይም በእንቁላል መጣያ ቦታዎች ላይ ጥቁር እና ቀይ ነጠብጣቦችን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።
ከዚህ የተነሳ ሬዲ ማይት በጊዜ ካልተከላከሉትና ካልተቆጣጠሩት በዶሮ እርባታ ሀብት ላይ ሙሉ በሙሉ ውድቀት ሊያመጣ የሚችል አደገኛ ተባይ በመሆኑ የዶሮ ቤቱን ንፅህና መጠበቅ እና ተስማሚ የሆኑ ማይት ማጥፊያ መድኃኒቶችን መጠቀም ያስፈልጋል።
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments