አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ችግኝ ከመትከል ባለ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ችግኝ ከመትከል ባለፈ ነው!፡፡

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23 ቀን 2018 (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


 
የኮሚሽኑ አመራር እና ሰራተኞች "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሞዴል አርሶ አደር አቶ ታደሰ ባልቻ ግቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
 
የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች እንደገለፁት አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ችግኝ ከመትከል ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ጤናማ የአየር ንብረት ለመፍጠር ሚናው የጎላ ነው፡፡
 
አያይዘውም አረንጓዴ አሻራ ማኖር የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል።
 
በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙ አመራሮች የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን በመከላከል አረንጓዴ አሻራ በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸው፤ መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን ታሪክ እየቀየረ መሆኑን ተናግረዋል።
 
በችግኝ ተከላው ላይ ያነጋገርናቸው የኮሚሽኑ፣ የክፍለ ከተማው እና የወረዳ 05 አመራርና ሰራተኞች እንደገለጹት በመርሃ-ግብሩ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች በሰፊው እየተተከሉ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና አለው ብለዋል።
 
የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች ይህ የዛሬው ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ለ2ኛ ጊዜ ያከናወኑት ሲሆን 3ኛ ዙር የ2018 ዓም አረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብርን በስኬታማ ሁኔታ ለመወጣት ከወዲሁ የተዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ሌላው በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ተሳታፊ የሆኑት አመራሮችና ባለሙያዎች ችግኞችን መትከል አንዱ ግብ ቢሆንም ተንከባክቦ ለጽድቀት ማብቃት፤ ከሁላችን የሚጠበቅ መሆኑን አሳስበዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments