በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን አገልግሎት የደንበኞችን...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን አገልግሎት የደንበኞችን እንግልት ይቀንሳል፡፡

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 24 ቀን 2018 (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በተደረገው የደንበኞች እርካታ ዳሰሳ ጥናት መሠረት፣ የዕርካታ መጠኑ 86 በመቶ መድረሱን ጥናቱ አመላክቷል።

ከደንበኞች ፍላጎት እና ጊዜው ከሚጠይቀው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ውጤታማነት አንጻር አሰራሮችን ይበልጥ እያሻሻሉና እያዘመኑ መሄድ ይገባል።አቶ ስለሺ ወርቅነህ (የአገልግሎት አሰጣጥና ክትትል ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር)::
ቴክኖሎጅን መሰረት በማድረግ ጊዜን፣ገንዘብ እና ጉልበት ቆጣቢ እንዲሆን መድረግ፣የአገልግሎት ሰጭውን የመፈጸም ብቃት ማጎልበት፤ አሰራሮችን ማሻሻል እና ተቋም መዋቅርን በማሻሻል ተደራሽነትን ማስፋት እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡

አገልግሎቶችን በመለየት ከቴክኖሎጅ ጋር ማስተሳሰር፣የሰራተኛውን ብቃት ማሳደግ፣የመረጃ አሰባሰብ፣አደረጃጀት፣አያያዝና አጠቃቀምን ማሻሻል ፣አሰራሮችን መከተል እና ለአሰራር ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን ለማሻሻል የቴክኖሎጅ አጠቃቀም ማደግ የሚጫዎተው ሚና ነው ብለዋል፡፡

አያይዘውም ሥነ-ምግባር እና የስራ ላይ ተግባቦት፣ሥነ-ልቦናዊ እና አእምሮአዊ ብቃት እና ሀብት አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት የሰራተኞችን የደንበኛ አያያዝ ክህሎት ለማዳበር እንደሚረዳ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የአገልጋይና ተገልጋይ የውይይት መድረክ ማካሄድ፣የተገልጋዮች የሀሳብ መስጫ ሳጥን እና የሀሳብ መስጫ እና መቀበያ ቴክኖሎጅ አቀፍ ፕላት ፎርም ማመቻቸት፣በሶፍትዌር የታገዘ መረጃ መለዋወጫ ዘዴ ተግባራዊ ማድረግ እና የዘመነ የክትትልና ድጋፍ እና ግምገማ አተገባበር ሥርአት መዘርጋት ከደንበኞች የሚሚሰጡ ግብረ-መልሶችን ተቀብሎ ፈጣን መፍትሄ ለመስጠት ወሳኝ መንገድ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments