“ተስፋን እንትከል!”
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
ዛሬ መላው ኢትዮጲያዊያን “ተስፋን እንትከል!” የሚለውን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል በነቂስ በመውጣት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ርብርብ እያደረጉ ይገኛል፡፡
አዲስ አበባ ከተማም የዚሁ አካል የሆነውን የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ተግባር እየፈፀመች ሲሆን የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አጠቃላይ አመራርና ሰራተኞችም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በመገኘት አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ “የምንተክላው ተስፋ አንድነታችንን፣ ሰላማችንን፣ እና ከፍ ሲል የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያረጋግጥ ለነገው ትውልድ የሚጠቅም ነው” ብለዋል፡፡
በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉት አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለዚህ ዕድል በቅተው በተከታታይ ዓመታት አሻራቸውን ማኖር በመቻላቸው ከፍተኛ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments