የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በተደረገላቸው ድጋፍ አመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ፡፡
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
በማህበር ተደራጅተው በትምህርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱ አርሶ አደሮች በተደረገላቸው ድጋፍ ተጠቅመው ከፍተኛ የሆነ ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ፡፡
የዮኒፋርም አካዳሚ ትምህርት ቤት ላይ ተደራጅተው እየሰሩ ካሉ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች መካከል የለሚ ኩራ ዮኒፋርም አካዳሚ ቀድሞ ከሚሰራበት በተጨማሪ አዲስ ቅርንጫፍ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ አካባቢ በመክፈት ዘርፉን እያስፋፋ ይገኛል፡፡
ዩኒፋርም አካዳሚ ኃላ/የተ/የህ/ስራ ማህበር በትምህርት የስራ ዘርፍ ላይ ቀላል የማይባል አስተዋጽኦ እያበረከተ ያለ እና አሁን ደግሞ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቡልቡላ ሪፌንቲ አካባቢ ተጨማሪ ቅርንጫፍ ከፍቶ ማስመረቁን ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
ም/ኮሚሽነሩ አያይዘውም በ2018 በጀት ዓመት ከ35 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ፣ 25 ሚሊየን ብር አካባቢ ወጭ፣ 10 ሚሊየን ብር ገደማ ትርፍ ማህበሩ ያገኘ መሆኑን ከትምህርት ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚገልጽ ተናግረዋል፡፡
ሌላው የዮኒፋርም አካዳሚ ኃላ/የተ/የህ/ስራ ማህበር አባላት ቀደም ሲል በነበሩት የትምህርት ተቋማት የታየው አበረታች የአፈጻጸም ውጤት፣ የካፒታል አቅም ማደግ እና የህብረተሰቡ የትምህርት ጥራት ፍላጎት ማደግ አዲሱን ቅርንጫፍ ለመክፈት ያስቻላቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡
አዲሱ ቅርንጫፍ በ2019 በጀት ዓመት ከ500 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን በመቀበል ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁንና ከ15 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር መሆኑን ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
አክለውም የግል ባለሀብቶችና ማኅበራት በግንባታና በንግድ ብቻ ሳይወሰን በትምህርት ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራታቸው ለሌሎች አርአያ የሚሆን ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments