ከተማ ግብርና ለአርሶ አደሮች ዘላቂ ልማት የማይተካ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ነሀሴ 1 ቀን 2018 (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በሥራ ዕድል ፈጠራ በከተማ ግብርና ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ በመደረጉ ዘላቂ የገቢ ምንጭ አንዲያገኙ እና የኑሮ ውድነትን እንዲቋቋሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ (የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ቡድን መሪ አቶ ለገሰ ወርቁ)፡፡
እንደ አቶ ለገሰ ወርቁ ገለፃ በኮሚሽኑ የሚሰጠው የቴክኒክ ድጋፍ፣ የሙያ ስልጠና፣ የግብዓት አቅርቦት፣ የገበያ ትስስር እና ተከታታይ የክትትልና ድጋፍ ተደራሽነት ተጠቃሚዎቹ በሥራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡
ከግብርናው ዘርፍ በተጨማሪ በንግድ፣ በአገልግሎትና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች የተሰማሩ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችም አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ቡድን መሪው ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል አቶ ለገሰ ወርቁ ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር ተጠቃሚዎች በማህበር እንዲደራጁ በማበረታታት፣ የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments