“የእንስሳት ሃብታችን የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

“የእንስሳት ሃብታችን የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት ነው።”

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም


የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ዛሬ በላቀ የቁርጠኝነት መንፈስና በዘመናዊ አካሄድ እየተቃኘ ይገኛል። ዘርፉን ከቀድሞው አሰራር በተለየ መንገድ በሳይንሳዊ መንገድ ማዘመን፤ የኑሮ ውድነትን ከመሰረቱ ለመቀልበስ፣ የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ኢኮኖሚ አሻራ ለማሳረፍ ሚናው ከፍተኛ መሆኑ በብዙ መልኩ ታይቷል፡፡


የእንስሳት ሃብት ልማትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችና በጥልቀት በተጠና ሙያዊ እና ቴክኒካል ድጋፍ ማገዝ፤ ከዘርፉ የሚገኘውን ምርትና ምርታማነት በበርካታ እጥፍ ያሳድገዋል። ይህ ጥረት የዜጎችን የዕለት ከዕለት ኑሮ ከማቃለል ባሻገር ኢኮኖሚያችንን ከስር መሰረቱ የሚገነባ ግዙፍ የለውጥ ማዕበል ነው።


በተለይም የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከተማ ግብርና ባህል እንዲሆን አበክሮ በመስራቱ ባለሙያዎች በቀጥታ ወደ ከተማ ግብርና ቤተሰብ በመዝለቅ በሚሰጡት የቅርብ ሙያዊ እና ቴክኒካል ድጋፍ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ፣ የዘር ማሻሻያ እና የመኖ ልማት ስራዎች ተቀይረዋል።


ሌላው በሳይንሳዊ አሰራር የታገዘው የእንስሳት እንክብካቤ የወተት፣ የሥጋ እና የእንቁላል ምርት እንዲጨምር በማድረግ ገበያው ላይ የሚታየውን የአቅርቦት እጥረት በብቃት እየተካ መጥቷል። ይኸም በቂና ጥራት ያለው ምርት ወደ ገበያ እንዲገባ በማድረግ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና የህብረተሰቡን ወርሃዊ ወጪ ማቃለል አስችሏል።


“የእንስሳት ሃብታችን የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት ብቻ ሳይሆን፣ የነገ ህልውናችን ማረጋገጫ ነው። ዘርፉን ስናዘምን የኑሮ ውድነትን እንሰብራለን፤ የምግብ ዋስትናችንን እናጸናለን።"


ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments