የመኸር ጊዜ፤ በዜማ የታጀበ የድካም ዋጋ!
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም
አየሩ ቀዝቀዝ ብሎ ማሳው በወርቃማ አዝመራ ደምቆ ሲታይ፤ አርሶ አደራችን የለፋበትንና የደከመበትን ዋጋ ለመቀበል በእንጉርጉሮ እና በፉከራ ወደ ማሳው ይዘምታል። የመኸር ወቅት ለሃገራችን ገበሬዎች ትልቁ የአዝመራ ጊዜ ነው፡፡
በዚህ ጊዜ አርሶ አደሩ ፈጣሪውን እያመሰገነ፣ በሬውን እያሞገሰ፣ “እረሰው እረሰው እረሰው በወይራ፤ አላየኸውም ወይ የሸመታን ተራ!”
እያለ እያንጎራጎረ አዝመራውን ያዘምራል። ላቡ በምድር ላይ ወድቆ፣ የፈጣሪን ጸጋ ከምድር እቅፍ ሊያፍስ ይተጋል፡፡
የግብርና ሥራችን አጋር ለሆኑት ጀግኖች አርሶ አደሮቻችን አክብሮታችን የላቀ ነው! መልካም የመኸር ወቅት ይሁንልን!፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments