ጊዜን በአግባቡ ስንጠቀምበት ጊዜ ይሸልመናል፡፡
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም
የጊዜ ዋጋ በግብርናው ዘርፍ፡- ወቅታዊውን የክረምት የግብርና ሥራ በሰዓቱ ያጠናቀቁ የከተማ ግብርና ቤተሰቦች በድህረ-ምርት ወቅት ያቀዱትን ያገኛሉ፡፡
በግብርና ሥራ ውስጥ የሰዓትና የወቅት ዋጋ ከፍተኛ እና የማይተካ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የምርት ዘመን ወቅቱን ጠብቆ በተከናወነ የቅድመ-ዝግጅት ሥራ እና በሰዓቱ በተጠናቀቀ የእርሻ መርሃ-ግብር ከፍተኛ ምርት መሰብሰብ ይቻላል።
የጊዜን በምንም ነገር የማይተካ ዋጋ በተመለከተ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ለኮሚሽኑ አጠቃላይ አመራርና ሰራተኞች ከግብርና ሥራችን እና ከነባራዊ ሕይወት ጋር በማጣጣም የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
የዋና ኮሚሽነሩን ንግግር ከኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነት አንፃር ስንመለከት የጊዜ ሚና በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ እና ግብርና ምንጊዜም ከወቅት ጋር የሚወዳደር በመሆኑ፣ "ጊዜን የጠበቀ ግብርና ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ቁልፍ ነው"፡፡
የግብርና ቤተሰብ የግብርና ሥራቸውን ወቅቱን ጠብቀው ከሰሩ ያልተጠበቁ የአየር ንብረት ለውጦችን በመቋቋም የተሳካ ምርት ማግኘት ይችላሉ።
እንደ ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ገለፃ ራሳችንን በመግራት ጊዜን በዕቅድ ስንጠቀምበት ጊዜ ራሱ በምናስመዘግበው ስኬት መልሶ ይሸልመናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments