በዘመናዊ ግሪን ሃውስ ቴክኖሎጂ እየለማ ያለ ድን...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በዘመናዊ ግሪን ሃውስ ቴክኖሎጂ እየለማ ያለ ድንቅ የግብርና ትሩፋት!


አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ


በአገራችን እየተስፋፋ የመጣው የግሪን ሃውስ (Greenhouse) ቴክኖሎጂ በግብርናው ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ይገኛል። በተለይም ያልተጠበቀ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን በመቋቋም በቁጥጥር ስር ውሎ የሚለማው ይህ ዘመናዊ አሰራር፣ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለበርካቶች የስራ እድል እየፈጠረ ነው።


በከተማችን አዲስ አበባ የግሪን ሃውስ ቴክኖሎጂ በተቋማት፣ በግለሰቦች እና በከተማ ግብርና ሰርቶ ማሳያና ግብዓት ብዜት ማዕከል ተሞክሮው እና ልምምዱ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡


ግሪን ሃውስ ውሃ ቆጣቢነቱን ስንመለከት ከባህላዊ የእርሻ ዘዴ በተለየ መልኩ ጠብታ የማጠጣት (Drip Irrigation) ቴክኖሎጂን በመጠቀም እስከ 70 በመቶ የሚደርስ ውሃን ይቆጥባል።


ከተባይና ከበሽታ መከላከል አንፃር ሰብሎች ከከባድ ዝናብ፣ ከበረዶ እና ከጎጂ ተባዮች ሙሉ በሙሉ ተጠብቀው እንዲያድጉ ያስችላል።


ዓመቱን ሙሉ ምርት ከማግኘት አኳያም የወቅት ገደብን በማስቀረት በማንኛውም ጊዜ ጥራቱን የጠበቀ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ለገበያ ማቅረብ ተችሏል።


ይህ ቴክኖሎጂ አርሶ አደሮች እና የከተማ ነዋሪዎች ከነስሰተኛ መሬት ከፍተኛ እና ጥራት ያለው ምርት እንዲያገኙ በማድረግ የኑሮ ማሻሻያ ማዕከል እየሆነ ይገኛል፡፡


ይህ ቴክኖሎጂ በከተማችን አዲስ አበባ በግብርናው ዘርፍ እየተገኘ ያለውን አበረታች እጅግ ዘመናዊ እርምጃ የሚያሳይ ድንቅ ማሳያ ነው።


ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments