የከተማ ግብርና፡ በአዲስ አበባ አዲስ ጎህ ሲቀድ
ዜና ትንታኔ
የከተማ ግብርና፡ በአዲስ አበባ አዲስ ጎህ ሲቀድ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ በፈጣን የዕድገት ሂደት ውስጥ ስትሆን፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የምግብ ሉዓላዊነትን እውን ማድረግ ለነገ የማይባል ተግባር ነው። በዚህ ረገድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከተማዋን ምርታማ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው።
የምግብ ሉዓላዊነት ማለት ማህበረሰቡ ጤናማ፣ በባህሉ የሚስማማ እና በራሱ አሰራር የተመረተ ምግብ በበቂ ሁኔታ የማግኘት መብት ሲሆን፤ የከተማ ግብርና በዚህ ረገድ የሚከተሉት ዋና ዋና ፋይዶች አሉት፦
በከተማው ውስጥ ባሉ ክፍት ቦታዎች፣ በዶሮ እርባታ፣ በግሪን ሃውስ (Greenhouse) እና በሽቅብ እርሻ (Vertial Agriculture) የሚመረቱ አትክልትና ፍራፍሬዎች የገበያ ዋጋን በማረጋጋት ለህብረተሰቡ ፈጣን የምግብ አቅርቦት እየፈጠሩ ይገኛሉ።
ምርቱ ከባለቤቱ በቀጥታ ወደ ሸማቹ (ተጠቃሚው) ስለሚደርስ የትራንስፖርት ወጪን እና የምግብ ብክነትን በእጅጉ የመቀነስ ሥራ እየተሰራ ይገኛል። ለዚህም የሰንበት ገበያዎች ጥሩ አስረጂ ይሆናሉ፡፡
ኮሚሽኑ በእንስሳትና በእጽዋት ሃብት ልማት አነስተኛ ቦታዎችን እና የተሸሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚከናወኑ የከተማ ግብርና ስራዎችን በማስፋፋት በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል።
ሌላው ግብርናው ከከተማው ውበት እና ሥነ-ምህዳር (Ecology) ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።
የከተማ ግብርና ራሱን የቻለ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመሆን አዲስ አበባ ከውጭ ከምታስገባው የግብርና ምርት አቅርቦት በመላቀቅ በራሷ አቅም እንድትመራ የሚያስችላትን የሉዓላዊነት መሰረት እየጣለ ይገኛል።
ከዚህ የተነሳ ዛሬ ላይ አዲስ አበባ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ በከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚዎችን አፍርታለች፡፡ ከ615 ሺህ ቶን በላይ ዓመታዊ የምርት መጠን ማምረት ችላለች፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments