የባዛሮች መከፈት ለነዋሪዎች አማራጭ ገበያ ከመፍ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የባዛሮች መከፈት ለነዋሪዎች አማራጭ ገበያ ከመፍጠር ባለፈ፣የደላላ ጣልቃ ገብነትን ያስቀራል፡፡


አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ


የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተከፈቱ ባዛሮች ለነዋሪዎች አማራጭ ገበያ ከመፍጠር ባለፈ፣ የደላላ ጣልቃ ገብነትን በማስቀረት ጥራት ያላቸው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ እያስቻሉ መሆኑ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በአስኮ ታክሲ ተርሚናል የተዘጋጀውን ባዛር መርቀው ከፍተዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ ኮሚሽነር ባዩ እንደገለጹት፣ የባዛሮቹ መከፈት ጥራት ያላቸው ምርቶች በአንድ ቦታና በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲዳረሱ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው።
በመሆኑም ይህንን መልካም ተሞክሮ እንደ አርአያ በመውሰድ መሰል የገበያ ማረጋጊያ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ምክትል ሥራ አስፈፃሚና የሥራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው በበኩላቸው፣ አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የተረጋጋ የገበያ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።
የባዛሩ መከፈትም ኅብረተሰቡን ያማከሉ ጥራት ያላቸው እና ቅናሽ የተደረገባቸው ምርቶች እንዲቀርቡ ከማድረግ ባለፈ ዘላቂ የገበያ ትስስርን ለመፍጠር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

በአስኮ ታክሲ ተርሚናል የተከፈተው ይህ የኤግዚቢሽን እና ባዛር መርሐ-ግብር እስከ በዓል መዳረሻ ቀናት ድረስ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments