ቃል በተግባር!

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

ቃል በተግባር!

አዲስ አበባ፤ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም


በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የሚሳተፉ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት በአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር በፓርቲው እሳቤ እና አሻራ  የተሰሩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጊጤ አዲስ አበባ ላይ መንግስት እየሰራቸው ካሉ በርካታ ሰው ተኮር ሥራዎች ውስጥ አንዱ አርሶ አደሮችን በዘላቂነት መልሶ ማቋቋምና ማልማት እንዲሁም ከተማ ግብርናን ማስፋፋትና ማጠናከር መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት ለዘመናት ተጨቁነውና ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን እና ቤተሰቦቻቸውን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋምና ለማልማት ከተገነቡት በርካታ ፕሮጀክቶች መካከል የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

ጉብኝቱን የመሩት የየቡድኑ መሪዎችም የከተማ ግብርና አዲስ አበባ ላይ በምግብ ራስን ከመቻል እና የኑሮ ውድነቱን ከማረጋጋት ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል።


የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ተሳታፊዎችም በተመለከቱት የልማት ሥራ መደሰታቸውን ገልፀዋል። በተለይም አርሶ አደሩ ከከተማዋ ልማት ጋር አብሮ እንዲለማ መደረጉ ለሌሎቻችን በተሞክሮነት የሚወሰድ ነው ብለዋል።

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አመራሮች፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎችም ጎብኝዎቹን በክብር ተቀብለው የተሰሩ ሥራዎችን አስጎብኝተዋል፤ ከከተማ ግብርና ከተገኘው ምርትም ለጎብኝዎቹ በከይነት መስተንግዶ አቅርበዋል።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ቃል በተግባር መሬት ላይ እየታየ መሆኑን ጎብኝዎቹ መመልከት እንዲችሉ አድርገዋል፤ ዞረው አስጎብኝተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments