ለ2019 ዘመን መለወጫ በዓል በቂ የሆነ የከተማ ግብርና መምርት እየቀረበ ይገኛል፡፡
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
የ2019 በጀት ዓመት አዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማርካት የሚያስችል በሁሉም ክፍለ ከተማና ወረዳዎች ላይ በቂ የከተማ ግብርና ምርቶች ለገበያ እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል 350,000 ሺህ እንቁላል ለገበያ የቀረበ መሆኑን የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ አሌክስ ደመቀ ገልፀዋል፡፡
መጭውን የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ እንደ ከተማ ከ17.92 ሚሊዮን በላይ እንቁላል እና 317,980 የሥጋ ዶሮ ለገበያ የቀረበ መሆኑን የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኒ ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም በገቢ ማስገኛ (Family Business) የተደራጁ፣ ማህበራት፣ ኢንተርፕራይዞች እና አምራች የግብርና ቤተሰቦች የከተማ ግብርና ምርታቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለገበያ እያቀረቡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ወተትና የወተት ተዋጽኦ እና የእርድ እንስሳትም ለበዓሉ በበቂ ሁኔታ እየቀረበ ሲሆን የአቅርቦትና የአጠቃቀም ሁኔታውን በተመለከተ ጥራቱ፣ ደህንነቱ እና ኃይጅኑ በተጠበቀ መንገድ ያለበት መሆኑንም አቶ መሐመድ አንስተዋል፡፡
ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው የምርት አቅርቦት በዓሉን ለማክበር ሊከሰት የሚችለውን የእንቁላልና የዶሮ ምርት እጥረትና የዋጋ ንረት በማረጋጋት የሸማቾችን ጫና በእጅጉ የቀነሰ መሆኑ ተረጋግጣል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments