“የማንሰራራት ቀን!”
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
ለመጭው አዲስ ዓመት በዓል የሚሆኑ የከተማ ግብርና ምርቶች ለሸማቾች በበቂ ሁኔታና በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ መሆኑ ተገለጸ።
የእንስሳት ተዋጽኦ፣ የሥጋ ዶሮ፣ እንቁላል እና በከተማ ግብርና የለሙ የተለያዩ የጓሮ አትክልቶች በቀጥታ ከአምራቹ ለሸማቹ በበቂ አቅርቦትና በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረቡ መሆኑን ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ገልፀዋል፡፡
አክለውም የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ገበያውን ለማረጋጋት 350,000 እንቁላል በተለያዮ የባዛር ቦታዎች ያቀረበ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደ ከተማ 18 ሚሊዮን እንቁላል ለገበያ የቀረበ ሲሆን እነዚህ የከተማ ግብርና ምርቶች በገበያው ላይ ሊፈጠር የሚችለውን የዋጋ ግሽበት በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ መሆኑን ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ተናግረዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments