ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ የሥጋ ምርት ለህብረ...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ የሥጋ ምርት ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከግብዓት አቅርቦት እስከ ምርት ስርጭት ባለው የምግብ ሰንሰለት ጥራትና ደህንነት ላይ ሰፊ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል።


በተለይም በከተማዋ በሚገኙ 3 የቄራ ድርጅቶች ከ40 በላይ ሥጋ መርማሪ ሀኪሞች በመመደብ የቅድመ እና ድህረ እርድ ምርመራዎች እየተደረጉ መሆኑን የሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ገልፀዋል።


ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ለሥጋ ወለድ በሽታዎች እንደሚያጋልጥ፣ ፍትኃዊ የንግድ ውድድርን እንደሚጎዳ፣ የውጭ ምንዛሪ ሊያስገኙ የሚችሉ ተረፈ ምርቶችን ለብክነት እንደሚዳርግ፣ አካባቢን እንደሚበክል እና የመንግሥት ገቢ እንደሚያሳጣ ም/ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡


አያይዘውም መጭውን የ2019 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የቄራዎች ምድረ ግቢ መጽዳት፣ የእርድ ክፍሎችና የእርድ መገልገያ መሣሪያዎች ንፅህና፣ የውኃና መብራት አቅርቦት፣ የሥጋ ማጓጓዢያ ተሽከርካሪዎች ዝግጅትን በተመለከተ የኮሚሽኑ የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ኳረንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ያሰማራቸው የባለሙያ ቡድን በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተከታተሉ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡


በመሆኑም ህብረተሰቡ ከልኳንዳ ቤቶች ሥጋ ሲገዛ በህጋዊ ቄራዎች መታረዱን ማረጋገጥ እንዳለበት አሳስበዋል። እንዲሁም ከህገ-ወጥ እርድ ራሱን በመቆጠብ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት ለኮሚሽኑ ጥቆማ በመስጠት በጋራ እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል፤ እንደ ወተት ያሉ ሌሎች የግብርና ምርቶችንም ጥራት አረጋግጦ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments