ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውርን ለ...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል፡፡


አዲስ አበባ፤ ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


በአዲስ አበባ ከተማ ከበዓላት ጋር ተያይዞ የሚፈጸም ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል።

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን መጭውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ለመንግስትና ለግል የሚዲያ ተቋማት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ኳራንቲንና የሪጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) መጭውን የዘመን መለወጫ በዓልና ተከትለው የሚመጡ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ህገ ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውርን ለመቆጣጠር የዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል ብለዋል፡፡

በከተማችን በሚገኙ በሦስቱ ቄራዎች ላይ የኮሚሽኑ የህክምና ባለሙያዎች በበዓል ወቅት የሚቀርብ ሥጋ ጥራትና ደህንነቱን የማረጋገጥ ተግባር እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘም ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውርን ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ኮሚሽኑ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ ህገወጥ የሆኑ ድርጊቶችን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል ጥቆማ መስጠት የሚጠበቅበት መሆኑንን አንስተዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments