ለአዲስ ዓመት በዓል በቁጥጥር የተረጋገጠና በቄራ...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

ለአዲስ ዓመት በዓል በቁጥጥር የተረጋገጠና በቄራዎች ምርመራ ሂደት ያለፈ የስጋ ምርት መሰራጨቱ ተገለጸ፡፡


አዲስ አበባ፤ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ



የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ዶ/ር ፀጋ ለማ እንዳስታወቁት፣ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሶስቱም ቄራ ድርጅቶች በተከናወነው ጥብቅ የቁጥጥር እና የፍተሻ ስራ የህብረተሰቡን ጤናማነት የጠበቀ ከፍተኛ የስጋ ምርት ለገበያ መቅረቡ ተረጋግጧል። በዚህም መሰረት ለዕርድ ከቀረቡት 5,511 እንስሳት መካከል በቅድመ እርድ ምርመራ ወቅት የታዩትን ደህንነት በመፈተሽ፣ ህግና መመሪያውን ያልሟሉ ጥቂት እንስሳት እንዲመለሱ ተደርጓል።

በሂደቱ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል በበሽታ ምክንያት የተመለሰ 1 ካርካስ ብቻ የተወገደ ሲሆን፣ ጤንነቱና ደህንነቱ ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠው 5,502 ካርካስ ደረጃውን በጠበቀ ተሸከርካሪ ለተጠቃሚው እንዲሰራጭ ተደርጓል። እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት ከሚውሉት ቆዳና ሌጦዎች መካከል 5,480 ያህሉ ደረጃውን አሟልተው ለአገልግሎት እንዲውሉ መላካቸውን ም/ኮሚሽነሩ አስታውቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments