በምግብ ሰንሰለቱ አስገዳጅ የጥራት ደረጃዎች ተግ...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

በምግብ ሰንሰለቱ አስገዳጅ የጥራት ደረጃዎች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ፡፡


አዲስ አበባ፤ መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


የማህበረሰቡን ጤና ከመጠበቅ ባለፈ የግብርና ምርቶችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የግብርና ምርት (የሥጋ፣ የወተት፣ የጥራጥሬ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች፣ …) ጥራትና ደህንነት ሊጠበቅ እንደሚገባ ተጠቆመ።

ቀደም ብለው ከነበሩት በተጨማሪ የህግ ማዕቀፍ ለሌላቸው ምርቶች አዳዲስ ማዕቀፎች እየተዘጋጁ ሲሆን፤ በሂደቱ ውስጥ ከወተት ምርቶች ጋር ተያያዥነት ያለው ረቂቅ ህግ ተዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል እንዲፀድቅ መላኩን የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት ከወተት ምርቶች ጥራትና ደህንነት ጋር በተያያዘ የላሞች ሸድ አሰራር፣ የላሞች ንጽህና አጠባበቅ፣ የወተት ማለቢያ፣ የወተት ማጠራቀሚያ፣ የወተት ማጓጓዣ፣ የወተት አላቢው ንጽህና፣ የወተት መሸጫና አጠቃላይ ከወተት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በስታንዳርድ የሚመራ መሆኑንም ም/ኮሚሽነሩ አያይዘው ገልፀዋል፡፡

የህግ ማዕቀፎቹ ሳይሸራረፉ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ሲውሉ የግብርና ምርቶች ከምርት እስከ ተጠቃሚው እጅ ድረስ ባለው ሂደት ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለዚህም ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ የከተማ ግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ ቅንጅታዊ ተቋማት ተሳትፎና የቁጥጥር ሥራ የተጠናከረ መሆን ይገባዋል፡፡

ይህ የቁጥጥር ሥርዓት የግብርና ምርቶችን ደህንነት በማረጋገጥ የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ እና የገበያ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይጫወታል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments