በቴክኖሎጂ  የተደገፈ   የግብርና  ሥራ የምግብ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በቴክኖሎጂ  የተደገፈ   የግብርና  ሥራ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ!


አዲስ አበባ፤ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


የግብርናውን ዘርፍ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በመደገፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽነትን ለማሳደግ በርካታ ተግባራት  ተከናውነዋል (የእጸዋት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ እንሰኔ)፡፡

በምርት ማከማቻና አሰባሰብ  ሰንሰለት ወቅት ሊደርስ  የሚችለውን ብክነት ለመቀነስ እና ለቀጣይ መፍትሄዎች መሰረት ለመጣል፣ የድህረ-ምርት አያያዝ ሥርዓት እየተዘረጋ መሆኑን አቶ ሲሳይ እንሴኔ ተናግረዋል።

 ይህ አሰራር የምግብ ደህንነት እና ጥራት  ስትራቴጂዎችን ወደ መሬት በማውረድ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አክለው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ሥነ-ምግብን ከምርት አያያዝ ጋር  በማስተሳሰር  የመጀመሪያዎቹን የልጅነት  ዕድገት ቀናት ጨምሮ  ማህበረሰቡ  የተመጣጠነ  ምግብ እንዲያገኝ  ከተለያዩ  ሴክተሮች እና ልማት አጋሮች ጋር የተቀናጁ ስራዎች በስፋት  እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments