ምርጥ ዘር ለተሻለ ምርትና ምርታማነት!

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ምርጥ ዘር ለተሻለ ምርትና ምርታማነት!


አዲስ አበባ፤ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


የተሻሻሉ ምርጥ ዘሮችና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሰብል እና የአትክልት ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የማይተካ ሚና ያላቸው በመሆኑ ከሚመለከታቸው የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የእጸዋት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  አቶ ሲሳይ እንሰኔ ገልፀዋል፡፡

 በግሪን ሃውስ እና በሃይድሮፖኒክስ ቴክኖሎጂ የታገዘ የግብርና ስራ በሰፊው በተቋማትና በግለሰብ ደረጃ ቤት ለቤት እየተሰራ መምጣቱ የምርትና ምርታማነት ማሳደጊያ ሌላኛው ዓይነተኛ ስኬት መሆኑንም ዳይሬክተሩ አክለው አንስተዋል፡፡

 ከዚህም በተጨማሪም በተያዘው የ2018/19 ምርት ዘመን ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ግብዓቶችን የማቅረብ ስራ በመከናወኑ በተያዘው በጀት ዓመት ከፍተኛ ምርት እንጠብቃለን ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments