የምርት እና ምርታማነት የማያቋርጥ ተግባር ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (የእ/ል/ል/ማ)
በእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል በዶሮ እርባታ የተሰማሩ ማህበራት በ2ኛ ዙር ያስገቧቸው ዶሮዎች የምርት ጊዜያቸውን አጠናቀው በመውጣታቸው 3ኛ ዙር እንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮዎችን እያስገቡ መሆኑን የማዕከሉ ሥራ አስኪጂ አቶ አሌክ ደመቀ ገልፀዋል፡፡
አንድ ማህበር ለዶሮ ኬጂ ጥገና፣ ለመኖ እና ለእንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ ግዥ ከ2.9 ሚሊዮን ብር በላይ በራስ አቅም ወጭ በማድረግ የተጀመረውን ምርትና ምርታማነት በተሻለ መንገድ ለማቅረብ እየሰሩ መሆኑንም አቶ አሌክስ ደመቀ አክለው ተናግረዋል፡፡
የ60 ቀን ዕድሜ ያላቸው ሎማን እንቁላል ጣይ 12,960 ቄብ ዶሮዎች አስከ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ከአለማ ፋርም በከፍተኛ የባለሙያ ክትትል ተገዝተው ወደ ማዕከሉ የገቡ መሆኑን ከሰጡን መረጃ ተመልክተናል።
አቶ አሌክስ አያይዘውም ቀሪ ቄብ ዶሮዎች በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙል ገብተው አስፈላጊው ሙያዊ ክትትል እንደሚደረግና የባዮሴኩሪቲ ጉዳይ ተጠብቆ ዶሮዎቹ የታቀደውን ምርት መስጠት እንዲችሉ እንደሚሰራ አንስተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments