የሰርቶ ማሳያና ግብዓት ብዜት ማዕከል በቴክኖሎጂ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የሰርቶ ማሳያና ግብዓት ብዜት ማዕከል በቴክኖሎጂ የታገዘ ተግባር!

 


አዲስ አበባ — መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


የከተማ ግብርና ሰርቶ ማሳያና ግብዓት ብዜት ማዕከል ዘመናዊ አሰራሮችንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በስፋት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ መሻሻሎችን እያስመዘገበ መሆኑን የማዕከሉ ሥራ አስኪጂ አቶ አብደታ ደሜ ገልፀዋል።
 
ባደረገው የማዘመን ስራ ነባር የአትክልትና ፍራፍሬ ዝርያዎችን ጠብቆ ከመያዝ ባለፈ፣ አዳዲስና ምርጥ የሆኑ ምርታማ ዝርያዎችን የማላመድና የማባዛት ስራዎችን በስፋት እያከናወነ መሆኑን ተመልክተናል።
 
ለዚህም ስኬት ማዕከሉ የቦታ ጥበብን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንሱ እንደ ሽቅብ እርሻ (Vertical Farming)፣ ዘመናዊ የግሪን ሃውስ (Greenhouse)፣ አኳፎኒክ እና ሃይድሮፎኒክ ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም የተቀናጁ የአፈርና የውሃ አጠቃቀም ስልቶችን በዋናነት እየተገበረ ይገኛል።
 
የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ያገኘናቸው የክፍለ ከተማ የእጽዋት ሃብት ልማት ቡድን መሪዎች እና የማዕከል ባሉሙያዎች ይህ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንቅስቃሴ ኮሚሽኑ የምግብ ሉዓላዊነትን እና የሥነ-ምግብ ሥርዓትን ለማረጋገጥ እየሰራ ላለው ሥራ ዓይነተኛ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
አስተያየት ሰጭዎቹ ማዕከሉ በቀጣይ አዳዲስ የዲጂታልና የዘመናዊ ግብርና ግብዓቶችን በማስተዋወቅ አቅሙን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባውም ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments