ጥራቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የሥጋ ምርት...

image description
- In አስተዳደር ዘርፍ    0

ጥራቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የሥጋ ምርት ማህበረሰቡ እንዲጠቀም ጥሪ ቀረበ!


አዲስ አበባ፤ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)


ለመጭው የመስቀል በዓል አከባበር የሚደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ ከህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውር ጋር በተያያዘ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገልጿል።

የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽ፣ ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ህብረተሰቡ በቄራ ተመርምሮ እና ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው አሽከርካሪዎች ብቻ የቀረበ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ንጽህናው የተጠበቀ የሥጋ ምርት እንዲጠቀም አሳስበዋል።

በሌላ በኩልም ሌሎች የግብርና ምርቶችን በተለይም የእንስሳት ተዋጽኦ የሆኑትን ለምሳሌ ወተትና ተያያዥ ምርቶችን ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ህብረተሰቡ መጠቀም እንደሚገባው ፀጋ ለማ (ዶ/ር) አንስተዋል፡፡

አያይዘውም የሚመለከታቸው አካላት ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል በየደረጃው ካለ የኮሚሽኑ መዋቅር ጋር እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።

ህብረተሰቡም ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውር ሲያጋጥመው በአቅራቢያው ለሚገኝ የህግ አካል ፈጣን ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት መልዕክት አስተላልፈዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments