የተጠናከረ የእንስሳት ጤና ክብካቤ ለተሻለ ምርትና ምርታማነት!
አዲስ አበባ፤ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
የተጠናከረ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ለምርትና ምርታማነት መሻሻል የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ከፍተኛ የእንስሳት ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ፋሲካ በለጠ ገልፀዋል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት የኒውካስትል በሽታ (NCD) ለመከላከል ብቻ በተሰራ ስራ ከ3.8 ሚሊዮን በላይ ዶሮዎች ክትባት መስጠት መቻሉንም ባለሙያዋ አያይዘው ተናግረዋል፡፡
በሌላበኩል ጉምቦሮ እና የዶሮ ታይፎይድና ኮሌራ ያሉ ክትባቶችም ከዕቅዳቸው በላይ የተፈፀሙ መሆኑን ዶ/ር ፋሲካ በለጠ አንስተዋል።
ከዶሮዎች በተጨማሪ ለቀንድ ከብቶች፣ ለጋማ ከብቶች፣ ለበግና ፍየል እንዲሁም ለውሾች የተጠናከረ የክትባትና የህክምና አገልግሎት በመስጠት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ የተቻለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዚህም መሰረት የአፍና የሰኮና በሽታ (FMD) ክትባት ከ43 ሺህ በላይ ዕቅድ ተይዞ ከ56 ሺህ በላይ በመፈጸሙ የላቀ ውጤት ታይቶበታል፡፡
ሌላው በውሾች ላይ የሚሰጠው የእብድ ውሻ በሽታ መከላከያ ክትባት ከ100 ሺህ በላይ ውሾች እንዲከተቡ ተደርጓል።
ይህንን በ2018 በጀት ዓመት የተመዘገበውን አመርቂ ውጤት በ2019 በጀት ዓመት የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከማዕከል እስከ ወረዳ ላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የአንድ ጤና ቅንጅታዊ ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑንም ዶ/ር ፋሲካ አንስተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments