ከ280 ኪ.ግ በላይ በህገ ወጥ መንገድ የታረደ ስጋ ተወረሰ!
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
ህገ-ወጥ እርድ ለህዝብ ጤና ስጋት የሚደቅን ተግባር ሲሆን፣ በባለሙያ ምርመራና ቁጥጥር ሳይደረግበት ለገበያ የሚቀርብ ሥጋ ለምግብ ወለድ ህመሞችና ለተለያዩ የጤና ጉዳቶች ሊያጋልጥ ይችላል። በመሆኑም ህገ ወጥ እርድን ለመከላከልና የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በተካሄደ የጋራ ቁጥጥር በቦሌ ክፍለ ከተማ ከ280 ኪ.ግ በላይ በህገ ወጥ መንገድ የታረደ ሥጋ ተወርሷል።
በአካባቢው በተካሄደ የጋራ ቁጥጥር 28 በግና ፍየል የታረደ 281 ኪ.ግ ስጋ እንዲሁም 41 የበግና የፍየል ቆዳዎች ተገኝተው ተወርሰዋል። ይህም ህገ ወጥ እርድን በመከላከል ህጋዊና የተቆጣጠረ የስጋ አቅርቦትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ቁጥጥር ወሳኝ መሆኑን ያሳያል።
ቁጥጥሩን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ግብርና ልማት ኮሚሽን እንዲሁም የፀጥታ አካላት በጋራ ያከናወኑት ሲሆን፣ የተለያዩ አካላት በቅንጅት መስራታቸው ህገ ወጥ እርድን በመቆጣጠር የስጋ ደህንነትን ለማረጋገጥ ያለውን ሚና ያጠናክራል።
በዚህም መሠረት ቅንጅታዊ ተቋማቱ ህገ ወጥ እርድን በጥብቅ በመከላከል፣ የሥጋ ንፅህናና ደህንነትን በጥብቅ በማረጋገጥ፣ የህብረተሰቡን ጤና ከሥጋ ወለድ ስጋቶች ለመጠበቅ ያላውቸውን ቁርጠኝነት በማጠናከር የሚያደርገውን ቁጥጥር በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል።
መረጃው፡- ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የትስስር ገጽ የተወሰደ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments