ወተት በሰው ልጅ አመጋገብ፣ ባህል እና ኢኮኖሚ...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

ወተት በሰው ልጅ አመጋገብ፣ ባህል እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ዋጋ አለው።


አዲስ አበባ፤ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)



የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል አንዱ የግብርና ምርት፣ ግብዓትና እና አገልግሎት ጥራቱ፣ ንጽናውና ደህንነቱ ተጠብቆ ለማህበረሰቡ እንዲቀርብ ማድረግ ነው፡፡

በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በዛሬው ዕለት የግብርና ምርት ጥራት፣ ኃይጅንና ደህንነት ከማስጠበቅ ጋር በተያያዘ በተለይም ከወተት ጋር ሰሞኑን በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተነሳ ያለውን የተሳሳተ መረጃ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐመድ ልጋኒ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚዎች ከተማችን ላይ መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡

ም/ኮሚሽነሩ በሰጡት መግለጫ ላይ አያይዘውም ከ615 ሺህ ቶን በላይ ምርት መድረሱን እና በቀጣይም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሰፊ ሁሉን አሳታፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ጥራትን የማስጠበቅ ሥራም እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ኳራንታይንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ከግብርና ምርት፣ ግብዓትና አገልግሎት ጋር በተያያዘ ከሚመለከታቸው አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ጥራቱን ደህንነቱን እና ንጽህናውን የማስጠበቅ ሥራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከዚሁ ጋር አያይዘው ከህገ-ወጥ እርድና ሥጋ ዝውውር ጋር በተያያዘ ሰፊ ሥራ እየተሰራ ሲሆን በሌሎቹም የግብርና ምርቶች ላይ ጥራትና ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ኃላፊነታችንን እየተወጣን ነው ሲሉ አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል ሰሞኑን ከወተት ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተነሳ ያለው ሃሳብ መሰረተቢስ መሆኑን እና ኮሚሽኑ የወተት ጥራት፣ ደህንነት፣ የገበያ ሰንሰለትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ደንብ ያዘጋጀ ሲሆን ወደፊት ፀድቆ ወደ ሥራ በሚገባበት ጊዜ ለማህበረሰቡ እና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ እንደሚሰራ አጽህኖት በመስጠት አንስተዋል፡፡

አክለውም ወተት በሰው ልጅ አመጋገብ፣ ባህል እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ዋጋ ያለው በመሆኑ ማህበረሰቡ ከላሞች ቤት እስከ ፍጆታ ድረስ ንጽህናውንና ደህንነቱን በጠበቀ አግባብ እንዲጠቀሙ ደንቡ ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል ደግሞ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments