በቀጣዮቹ 90 ቀናት ከ141 ሺህ በላይ ነዋሪዎች...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

በቀጣዮቹ 90 ቀናት ከ141 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል።

 


አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)



​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ክላስተር የ90 ቀናት የንቅናቄ ዕቅዱን ይፋ በማድረግ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
 
​በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ግምገማ የቀረበ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት (90 ቀናት) የሚከናወኑ ዋና ዋና የንቅናቄ ዕቅዶች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
 
​የንቅናቄ ዕቅዱ ዋና ዋና ትኩረቶች፦
 
​​የከተማ ግብርናና የምግብ ዋስትና፦ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ነባር የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን ዘላቂነት ከማረጋገጥ ባሻገር፣ 36,463 አዲስ ቤተሰቦችን በፋሚሊ ቢዝነስ መርሃ-ግብር ተጠቃሚ ለማድረግ አልፎም በዘርፉ ለ12,670 ዜጎች አዲስ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል።
 
​የምርት አቅርቦትና የኑሮ ውድነት፦ የኑሮ ውድነቱን ለማስታገስ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የእንስሳት ግብዓቶች፣ ቴክኖሎጂዎችና መኖዎችን በማቅረብ በአጠቃላይ 230,612.87 ቶን ምርት ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል።
 
የሥራ ዕድል ፈጠራ፦ በከተማዋ ያለውን የሥራ አጥነት ምጣኔ ለመቀነስ በተቀረጸው ዕቅድ፤ በህብረተሰብ ግንዛቤ ፈጠራ፣ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (LMIS) ምዝገባ እና በክህሎት ማበልጸጊያ ሥልጠናዎች አማካኝነት ለ141,347 ነዋሪዎች ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል።
 
​የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ፦ ከ1,000 በላይ ለሚሆኑ ኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታዎችን በኪራይ ማስተላለፍ፣ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አቅርቦት ማመቻቸት እና 514 ኢንተርፕራይዞችን ወደ የተሻለ የዕድገት ደረጃ ማሸጋገር ሌላው የትኩረት አቅጣጫ ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments