የተቀናጀ ከተማ ግብርና ለሁለንተናዊ ብልጽግና!
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
የተቀናጀ ከተማ ግብርና (Integrated Urban Agriculture) በከተሞች ውስጥ የሚገኙ ባዶ ቦታዎችን፣ ጣራዎችን እና አነስተኛ ቦታዎችን በመጠቀም የእፅዋት ልማትን፣ የእንስሳት እርባታን ስራዎችን አስተሳስሮ ማከናወን ነው።
ይህ የግብርና ዘርፍ ከተሞች ከሚያመነጩት ተረፈ-ምርት ሃብት በመፍጠር (ለምሳሌ የምግብ ተረፈ-ምርት እና የእንስሳት ጽዳጅን ወደ ኮምፖስት እና ባዮ ጋዝ በመቀየር) የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ የስራ ዕድል ለመፍጠር እና የአካባቢን አየር ንብረት ለመጠበቅ ትልቅ ሚና አለው።
በዛሬው የመስክ ምልከታችን በቦሌ ክፍለ ከተማ የነዶክተር ረጋሳ ጉርሙ እና ኤርምያስ ረጋሳ የተቀናጀ ከተማ ግብርና ልማት ተዘዋውረን ተመልክተናል፡፡ እየተሰራ ያለው ከተማ ግብርና ሥራ የተቀናጀ ከመሆኑም በላይ ለሌሎች አስተማሪ የሆኑ ተግባራት አሉት፡፡
ለአብነት ይህንን ተመለከትን እንጅ ከተማችን አዲስ አበባ በዚህ ዘርፍ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣችበት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ተሳታፊና ተጠቃሚዎችንም በከተማ ግብርና ተጠቃሚ ማድረግ ችላለች፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments