በምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍትኔት የተደራጁ የዶ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍትኔት የተደራጁ የዶሮ እርባታ ማኅበር አባላት አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸውን ገለጹ።

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)



በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም በዶሮ እርባታ ሥራ የተሰማሩ ማህበራት በዘርፉ በመሰማራታቸው አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ እንደሚገኙ ከክፍለ ከተማው የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ከእነዚህ ማኅበራት መካከል በክፍለ ከተማው ወረዳ 04 አስተዳደር በምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍትኔት መርሃ-ግብር የተደራጁ  ታረቀኝ፣ አሠለፈች እና ጓደኞቻቸው የዶሮ ሽርክና ማኅበር በዶሮ እርባታ ሥራ ስኬታማ አፈጻጸም እያሳዮ መሆኑን የክ/ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ደመቁ ንጉሴ የላኩልን መረጃ ያሳያል።

የሽርክና ማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታረቀኝ ርኬቦ ያዩ ማኅበሩ ከዶሮ እርባታው በየቀኑ እስከ 900 እንቁላሎች ማግኘት መቻሉን ገልፀው  ይህም ማኅበሩ በምርት መጠን ረገድ እያሳየ ያለውን አበረታች ለውጥ የጋራ ሥራ ውጤታማነት የሚያመለክት መሆኑን ተናግረዋል፤ በማለት ወ/ሮ ደመቁ መረጃውን አድርሰውናል።

ይህ የምርት መጠን በገበያ ላይ የሚኖረውን የእንቁላል አቅርቦት ከመደገፉ ባሻገር፣ የማኅበሩ አባላት የገቢ ምንጭ በመሆን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም  ማህበሩ ገልጿል።

የሽርክና ማኅበሩ አባላት በጋራ በመሥራት የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል፣ የገቢ ምንጫቸውን ለማሳደግና ራሳቸውን በኢኮኖሚ ለመደገፍ በትጋት እየሠሩ እንደሆነ ኃላፊዋ አንስተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments