ቀልጣፋ የቅሬታ አፈታትና የህግ የበላይነት ለተቋማዊ እምነት!
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
ህጎችና መመሪያዎችን መሠረት ያደረገ ቀልጣፋ የቅሬታ አፈታት ሥርዓት መዘርጋት ለተገልጋዮች እምነት መጎልበት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡
የቅሬታና አቤቱታ አቀባበልና አፈታት የህግ ምክር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ በዳዳ ውሳኔ ለመስጠት አጠራጣሪና ውስብስብ የሆኑ ቅሬታና አቤቱታዎች ሲያጋጥሙ ከቅርብ ኃላፊ ጋር በመነጋገር ህግና መመሪያን መሰረት በማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም የህግ የበላይነትን በመከተል ቅሬታ አቅራቢዎች አፋጣኝ ምላሽ አግኝተው በተቋሙ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጠነክር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አቤቱታቸውን በአግባቡ መግለጽ ለሚቸገሩ ተገልጋዮች ቅድሚያ የምክር አገልግሎት በመስጠት በቃልና በጽሑፍ አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው በህጉ አግባብ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚደረግ አንስተዋል።
ሌላው የቀረበው ቅሬታ ወይም አቤቱታ ከተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት ውጭ ሲሆን ወይም ሌላ አማራጭ አሰራር የሚጠይቅ ከሆነ ደግሞ ተገልጋዩ ጉዳዩን እንዴት መፍታት እንዳለበት ግልጽ መመሪያ ተሰጥቶት ወደሚመለከተው አካል ይመራል ብለዋል።
የተለያየ መልክና ይዘት ያላቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በቅሬታና አቤቱታ መልክ በተገልጋዮች በኩል የሚቀርቡ ሲሆን እንደየ አመጣጣቸው ህግና ህግን ብቻ መሰረት ባደረገ አግባብ ምላሽ የሚሰጥባቸው መሆኑን አቶ ታደሰ በዳዳ ገልፀዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments