የማህበራትን ምርታማነት ለማሳደግ በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም (አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ)
በ2017 እና በ2018 በጀት ዓመት ተደራጅተው የፋይናንስ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ሥራ ለገቡ ማህበራት ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ውጤታማ እንዲሆኑ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ቡድን መሪ አቶ ለገሰ ወርቁ ገልፀዋል፡፡
አክለውም ማህበራት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ የክህሎት ክፍተታቸውን በመለየት ስልጠናዎችን ለማመቻቸት የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ በማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የተጠናቀቁ መሆኑን ተናግረዋል።
ለማህበራት የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ፣ ብድራቸውን እንዲመልሱ በማበረታታት ምርትና ምርታማነታቸውን የማሻሻል ሥራ እየተሰራ መሆኑን ቡድን መሪው አያይዘው አንስተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments